በስንዝሮ ተረክ፤ ታሪክ እና ትዝታ

Authors

  • ይድነቃቸው ሰለሞን እንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነጽሑፍ ትምህርት ክፍል ፣ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

DOI:

https://doi.org/10.20372/ajcik.2023.2.1.931

Abstract

የዚህ ጥናት አላማ በአዳም ረታ ‹‹የስንብት ቀለማት›› ውስጥ የመጣውን ስንዝሮ ‹‹በሃዲስ ታሪካዊነት›› እና ‹‹በትዝታ›› መታገጊያነት መፈከር ነው፡፡ ይህም ጥናቱን እስካሁን የደራሲው ሥራዎች ባልታዩበት የባህል እና የትዝታ ንድፈ ሃሳቦች አንጻር የተሰናዳ አድርጓታል፡፡ ሃዲስ ታሪካዊነት ባህል መር የሥነ-ጽሑፍ ሃተታ ማቅረቢያ ስልት ሲሆን ትዝታ እረፍት ያለው (የተረጋጋ) ሥነ-ልቦናዊ ሁኔታን የሚያስረዳ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ የትዝታ ሃተታ የሃገር ቤቱን ከባህር ማዶ፣ ያለፈውን ከአሁን ነባራዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም ህልምን ከአዘቦታዊ ጋር እየቀየጠ ተረክን ለመከወን የሚረዳ ጽንሰ ሃሳብ ከመሆኑም ባሻገር በሽግግር ጊዜ የሚከሰትን መናጋት በተስፋ ለማለፍና ለህይወት ትርጉም እንዲኖረን፣ እና ማህበራዊ ግንኙነት እንዲጎላ ብቸኝነት እንዲሳሳ የረዳ እሳቤ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ አላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴን በመጠቀም የጥናቱን አላማ ከግብ ለማድረስ የረዱ ገጸንባቦች (texts) ተመርጠው እና በንድፈ ሃሳብ ዳብረው ትንታኔ ቀርበዋል፡፡ ጥናቱ በሁለት ክፍል የቀረበ ነው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል በስንዝሮ የቀረበ ሃዲስ ታሪካዊ ሃተታ በሚል ንዑስ አርዕስት የተሰናደ ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ደግሞ በስንዝሮ የቀረበ የትዝታ ሃተታ በሚል አርዕስት ሥር የቀረበ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ወረቀት በ‹‹የስንብት ቀለማት›› ውስጥ የተከሰተውን ስንዝሮን በመውሰድ ባህልን መሰረት ያደረገ ትንተና እና እንዲሁም የስንዝሮ ትዝታ መምጣት ለተረበሸው ማህበረፖለቲካ እና ለታጎለው ሥነ-ልቦና (አጠቃላይ ለባህሉ) ረፍት የመስጠት አብርክቶ እንደሚኖረው እንመለከትበታለን ማለት ነው፡፡

Keywords:

የስንብት ቀለማት፣ , ስንዝሮ፣ , ሃዲስ ታሪካዊነት፣ , ትዝታ

Downloads

Published

2023-06-30

How to Cite

ሰለሞን ይ. (2023). በስንዝሮ ተረክ፤ ታሪክ እና ትዝታ. Abyssinia Journal of Culture and Indigenous Knowledge, 2(1), 10–24. https://doi.org/10.20372/ajcik.2023.2.1.931

Issue

Section

Articles